ከሶስት መቶ ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ይገኛል የሚባለው Hepatitis B ሔፓታይትስ ቢ ቫይረሰ ዋና የጉበት በሽታ ጠንቅ ነው፡፡ ጉበት መስራት አስከሚያቆም ወይም በቫይረሱ ምክንያት የጉበት ካንሰር አስከሚከሰት ድረስ ድምጽ አልባ የጉበት በሽታ ሥር እየሰደደ የሚሄድበት ሁኔታ ነው፡፡ ደግነቱ መከላከል ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከዚያ በፊት በቫይረሱ መያዘና አለመያዝን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ቫይረስ በታዳጊ አገሮች በብዛት የተሠራጨ በቤተሰብ ሊዛመት ሰለሚችል ሰለ ሔፓታይትሰ ቢ መገንዘብ ወሳኝ ነው፡፡ ቪዲዮውን ይመልከቱ እርስዎም ይማሩበታል፡፡
HIV ኤች አይ ቪ አሁንም አለ፡፡ ሥርጭቱ የቀነሰ ቢመስልም ባንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች መዛመቱ አልቀረም፡፡ በመድሀኒቶች ምክንያት በሽታም እንዳይከሰት በማድረግ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ረዥም ዕድሜ እየኖሩ ነው፡፡ ያ ግን መድሐኒቱ ሲገኝ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን አለመያዝ አይሻልም? በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለቫይረሱ በድንገት ቢጋለጡ ቫይረሱ ወደ ሰውነት ስር እንዳይሰድ መከላከል ይቻላል፡፡ በመድሀኒት፡፡ አሁን ግን በስድስት ወር አንድ ጊዜ ብቻ በሚሠጥ አስቀድሞ መካለክል የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡ ጉዳዩ በግል ባይመለከትዎ እንኳን ሌሎችን መምከርና ማሰተማር ይችላሉ፡፡
ወላጆቻችን ወይም አያቶቻችን በሳይንሳዊ መንገድ ባይነግሩንም በየቀኑ የፀሀይ ብርሃን መሞቅ ለጤንነት ጥቅም እንዳለው ያውቃሉ፡፡ የፀሀይ ብርሃን ከሚታወቀው የቫይታሚን ዲ እና የአጥንት ጥንካሬ በተጨማሪ በደም ውስጥ የስኳር መጠንን መቀነስ እንደሚችል ሳይንሳዊ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ እንግዲህ ሌላም ጥቅም ሊኖረውም ይችላል፡፡ ለማንኛው ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ ለሌችም አጋሩ፡፡
በዕድሜ ምክንያት መዘንጋት ወይም መርሳት የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ውጭ ዋናው ምልክቱ መርሳት ሳይሆን ባጠቃላይ የአዕምሮ መሳትን የሚያሰከትለው አልዛይመር የሚባል በሸታ አለ፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት ይህንን የአእምሮ መዘንጋት ወይም መርሳት ማዘግየት ወይም ቀደም ብሎ እንዳይከሰት ምን ቢደረግ ይሻላል ለሚለው ጥያቄ መልስ፣ አለም አቀፋዊ ጥናት ተደርጎ መረጃ ወጥቷል፡፡ ከጥናቱ ዋና መሪና በዚህም ጥናት ተሸላሚ ከሆኑት ፕሮፌሰር ጋር የተደረገውን ውይይት ይመልከቱ፡፡ የባህሪ ለውጥ ማምጣት እርጅና ጎራ ውስጥ ሳይገቡ የሚደረግ ነው፡፡ ሰለዚህ ይህ ትምህርቱ ለሁሉም ዕድሜ ክልል አዋቂዎች ነው፡፡ በርግጠኛነት ይማሩበታል፡፡
Copyright © 2026 Gosh Hagere - All Rights Reserved.