ሰለ ስኳር በሽታ ስንነጋገር ሁለት አይነት መኖራቸውን መገንዘብ አለብን፣ አይነት አንድና አይነት ሁለት ይሏቸዋል፡፡ (Type 1 and Type 2))፡፡ በዚህ ርዕስ የምንመለከተው አይነት ሁለት ሰለተባለው ነው፡፡ ይህም በአዋቂ ሰዎች ላይ የሚከሰት በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህ በአዋቂዎች ላይ የሚከሰተው አይነት ሁለት የስኳር በሸታ ሊከሰትባቸው የሚችሉ ሰዎች ተብሎ የተለያዩ ምክንያቶች ይዘረዘራሉ፡፡
· ከመጠን በላይ ውፍረት
· ዕድሜ 45 አመትን ከዛ በላይ
· በቤተሰብ ውስጥ የስኳር በሽታ ካለ (በሥጋ ዝምድና) ወይ በዘር
· የጥቁር ዝርያ
· የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች
· ሴቶች ከሆኑ ከርግዝና ጋር የተያያዘ የስኳር በሽታ ተከስቶባቸው ከሆነ
· የሰውነት እንቅስቃሴ የማያዘወትሩ ከሆነ
· በደም የኮለሰትሮል ምርመራ ላይ ጤናማው ኮለስትሮል (HDL) ዝቅተኛ ከሆነ ወይም ጮማ (Triglyceride) ከፍ ያለ ከሆነ
· የልብ ህመም ኖሮት የሚያውቅ ከሆነ
· አንገትዎ ወይም ብብትዎ አካባቢ ቆዳዎ ላይ ጠቆር ያለ እንደ ከፋይ የመሰለ ምልክት ካለዎት (በእንግለዝኛ Acanthosis Nigricans) ይባላል
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ፣ በአብዛኛው የስኳር በሽታ የሚጀምራቸው ሰዎች፣ አብዛኞቹን አያሟሉም፡፡ እንዳውም ከሰውነት ውፍረት ይልቅ ቀጠን ያሉ ናቸው፡፡ በአብዛኛው፡፡ እናም፣ ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን፣ ከዚህ ጋር የተያያዘ የምግብ አይነት ይኖር የሚሆን የሚሉ ጥያቂዎች ደጋግመው ይነሳሉ፡፡ ከነዚህ መሀል፣ አንዱ ትኩረት የሠጠሁበት ነገር ቢኖር የምግብ ዘይት ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ አገሪቱ የራሷን የምግብ ዘይት በማምረት ለዜጎቿ ማቅረብ የምትችል ብተሆንም፣ የምግብ ዘይት ከውጭ እንደሚገባ ይታወቃል፡፡ ታዲያ እንዴት ነው በማለት ጥናቶችን ስከታተል፣ በቻይና ይህንን በተመለከት ያቀረቡትን የጥናት ውጤት አገኘሁ፡፡ ህም፣ ይህንስ ለወገን ማካፈል ጥሩ ነው አልኩ፡፡
ጥናቱ አላማ ያደረገው፣ በቻይና በሀገረ አቀፍ ደረጃ፣ የምግብ ዘይት አጠቃቀምና የስኳር በሽታ መከሰት ግንኙነት እንዳለው ለማየት ነበር፡፡ በሽታው የነሱም ችግር ነው ማለት ነው፡፡ እንደተለመደው በመረጃ የተደገፈ ጥናታዊ ግኝት ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡
ባጠቃላይ 15022 ዕደሜያቸው ከ20 አመት በላይ የሆኑ ዜጎች ከቻይና ኒውትሪሽን ሰርቬይ የተመለመሉ ሲሆን፣ እነዚህ ሰዎች በ1997፣ 2000፣ 2004፣ 2006 ወይም 2009 ተመልምለው እሰክ 2011 አ.ም ድረስ ክትትል ሲደረግ የቆዩ ናቸው፡፡ ሰዎች ወድ ክትትሉ ፕሮገራም ሲገቡ፣ የስኳር በሽታ እንደሌለባቸው አስመዝገበዋል፡፡
አነዚህ ሰዎች የሚጠቀሙት የምግብ ዘይት አይነቶች ማለትም ከጮማ የተሠራ ዘይት(lard oil)፣ የኦቾሎኒ ዘይት (Peanut oil)፣ ካኖላ፣ ሶይቢን፣ ሰሊጥ (sesame oil)፣ ከአትክልቶች ተጣርቶ የተሠራ ዘይት (refined blended plant oil) በየጊዜው ሪከርድ እንዲያዝ ተደርጎ፣ ሰዎች የሚጠቀሙት ወይም የሚመገቡት የዘይት አይነት አማካይ መጠን በስሌት እንዲታወቅ ተደረገ፡፡ የተለያዩ የስታቲሰቱክ መመርመሪያዎችን በመጠቀምና በማስላትም የስኳር በሽታ ቁጥር ሁለት መንስኤ ሰበብ ወይም ምክንያት ናቸው ወይም አይደሉም ለማለት አሁንም ሌላ ስሌት ተጠቅመው ውጤቱን አካፈሉን፡፡
አታካች የሆነውን ዝርዝር የስታቲሰቲክ ቁጥሩን ልለፈውና፣ የጥናቱን ማጠቃለያ ላጋራችሁ፡፡ በጥናቱ ወይም በክትትሉ ከነበሩ ሰዎች ለ14 አመታት በተደረገው ክትትል 1014 ሰዎች የስኳር በሽታ ተከስቶባቸዋል፡፡
አጥኝዎቹ የሚሉት፣ ከጮማ የተሠራ ዘይት፣ የቦሎቄ ዘይት፣ ከአትክልቶች የተሠራ የተጣራ ዘይት መጠቀም ለስኳር በሽታ ቁጥር ሁለት መከሰት ከፍተኛ ምክንያት ናቸው፡፡ በአንፃሩ ሌሎቹን የዘይት አይነቶች የሶይቢን፣ የሰሊጥ፣ ካኖላ ዘይት ከስኳር በሽታ መከሰት ጋር ግንኙነት የላቸውም ይላሉ፡፡ የምግብ ዘይት መጠቀምን ቀንሱ የሚለው ምክር የመጣው፣ ዘይት የሚመገቡ ሰዎችን ጭራሽ ዘይት ከማይጠቀሙ ሰዎች ጋር በማወዳደር ያገኙትን ውጤት በመገንዘብ ነው፡፡ ዘይት የማይጠቀሙ ሰዎች እንዴት ነው፡፡ እንደዚሀ ከሆነ ዘይት ተወደደ ሲባል፣ የራሱ ጉዳይ ያስብል ይሆን?
ጥናቱ ለቻይኖችና ምክሩም ለቻይኖቹ ቢሆንም፣ ማካፈሉ ይበጃል፡፡ ባጠቃላይ የምግብ ዘይት አጠቃቀማቸውን እንዲቀንሱ ነው የሚመክሩት፡፡
ከዚህ ቀደም ፍሩክቶስ የሚባል የስኳር አይነት ከስኳር በሽታ ጋር ግንኙነት እንዳለው በጎሽ ድረ ገፅ አስፍረያለሁ፡፡
ለማንኛውም የምተጠቀሙትን የምግብ ዘይት አይነት ማስተዋልም ጥሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምግብ ዘይት ከውጭ ማስገባቷ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ መንግሥት አስቦ ፖሊሲ እሰከሚቀይር መጠበቅም ተገቢ አይደለም፡፡ እንዳውም ህብረተሰቡ በረጋ መንገድ ጥያቄና ጫና በመፍጠር ፖሊሲ ማስቀየር ይኖበታል፡፡ ሀገር በቀል የሆኑ ዘይቶች ጤናማ እንደሆኑ ነው የሚገመተው፡፡
የስኳር በሽታ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ በከፈተኛ ቁጥር እየጨመረ 425 ሚሊዮን ሰዎች በሸታው ያለባቸው ሲሆን፣ ሌሎች 352 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ ሌሎች ጥናቶችም የሚጠቁመት የአመጋገብና የአኗኗር ለውጥ ነው፡፡ የምዕራባውያን አመጋገብ መጠቀምና እንቅስቃሴ አለማዘውትር ችግር አለው፡፡
እንቅስቃሴ ውስጥ በእግር ረዘም ያለ መንገድ መሄድ ጠቀሚታም አለው፡፡ አግረኝነቱ ጥቅም አለው ማለት ነው፡፡ ለጤና ሲባል ቅርብ ቦታዎችና በአግር ማስነካቱ ገንዘብም ያድናል፡፡
መልካም ንባብ፡፡
ዋቢ
Zhuang et al, Cooking oil consumption and type 2 diabetes 1805
Copyright © 2026 Gosh Hagere - All Rights Reserved.